ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ አትላንታ ጆርጂያ ቀጥታ የመንገደኞች በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 13/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ አትላንታ ጆርጂያ ቀጥታ የመንገደኞች በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ወደ አትላንታ ጆርጂያ የሚያደርገው በረራም በሳምንት አራት ቀናት መሆኑንም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ ጆርጂያ የሚጀምረው አዲስ ቀጥታ በረራ በሰሜን አሜሪካ  ከዋሺንግተን ዲሲ፣ ኒዋርክ፣ ኒው ዮርክ እና ቺካጎ በመቀጠል አምስተኛ መዳረሻው መሆኑንም ጨምሮ አስታውቋ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም