ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው በጥር ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የነዳጅ ማስተካከያ ዋጋን መነሻ በማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የአገልግሎት መስጫ ታሪፍ ላይ ጥናት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቁሟል፡፡

የጥር ወር ነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍን ማሻሻያ ጥናት መደረጉ ይታወሳል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች÷ የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣ ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም