አቶ ሞገስ ባልቻ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ ሞገስ ባልቻ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆኑ
አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 12/2015፦አቶ ሞገስ ባልቻ ገብረመድህን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆኑ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቶ ሞገስ ባልቻ ገብረመድህንን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አድርገው መሾማቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።