ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ
አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 12/2015፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን ሹመቶች እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፦
1. ዶ/ር አለሙ ስሜ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
2. ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር
3. ዶ/ር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትርበተጨማሪም
ከጥር 10/ 2015 ጀምሮ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰተዋል
፦1. አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ
2. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር
5. አቶ መለሰ አለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ