የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴቱ ባለፈ በአገር ሃብትነቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው- የሃይማኖት አባቶች - ኢዜአ አማርኛ
የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴቱ ባለፈ በአገር ሃብትነቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው- የሃይማኖት አባቶች
አዲስ አበባ (ኢዜአ)ጥር 11/2015 የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴቱ ባለፈ በአገር ሃብትነቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ።
የጥምቀትና ከተራ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል ይጠቀሳሉ።
የጥምቀት ክብረ-በዓል ባለው ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበ የኢትዮጵያ ሃብት መሆኑም ይታወቃል።
የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሃይማኖት አባቶች የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ይዘትና የሚከበርበትን ምክንያት ያስረዳሉ።
በዓሉ የኢትዮጵያ ሃብትና የዓለም ቅርስ በመሆኑም ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶች ተጠብቀው ሊዘልቁ ይገባል ይላሉ የሃይማኖቱ አባቶች።
በመሆኑም የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴቱ ባለፈ በአገር ሃብትነቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።
የጥምቀት በዓል አከባበር የአንድነት፣ የሰላም፣ የፍቅር ማሳያም በመሆኑ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ብለዋል።
የበዓሉን ይዘትና ትውፊት በማስጠበቅ ለዓለም በማስተዋወቅ የአገር መገለጫና የጋራ ሃብታችን አድርገን መቀጠል አለብን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።