ቀጥታ፡

እርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ ጥምቀትን በአብሮነትና በደስታ በማክበራችን ተደስተናል- የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች

ጥር 11/ 2015 (ኢዜአ) ለዓመታት እርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ ጥምቀትን በአብሮነትና በደስታ በማክበራችን ተደስተናል ሲሉ የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ አክሱም ከተማና ሌሎችም የትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በአክሱም ከነበሩት የበዓሉ ታዳሚዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ምዕመናን በዓሉን በሰላምና በተረጋጋ መልኩ በማክበራችን ልዩ ስሜት አሳድሮብናል ብለዋል።

May be an image of 5 people, people standing and outdoors

ከሁለት ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ችግር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሕዝቡ ለምስቅልቅል ህይወት መዳረጉን ተናግረዋል።

በመንግሥትና የህወሓት ታጣቂዎች የሰላም ስምምነት ከተፈጠረ በኋላ ግን የሰላም አየር አግኝተናል በዚህም ተደስተናል ብለዋል።

በዘንድሮው የጥምቀት በዓል አከባበር ለዓመታት እርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ በአብሮነትና በደስታ በማክበራችን ተደስተናል ሲሉም ተናግረዋል።

May be an image of 8 people, child, people sitting, people standing and outdoors

የተጀመረውን ሰላም ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ሁላችንም የሚጠበቅብንን አደራ እንወጣለን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም