ቀጥታ፡

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ኢዜአ ጥር 11/2015- የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓልን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች በልደታ ማሪያም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው።

በበአሉ ላይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሁነቶች በቅዳሴ ፣ በፀሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ሲሆን በቦታውም የሃይማኖት አባቶች ፣የእምነቱ ተከታዮች ምዕምናን እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል ።

May be an image of 3 people, people standing and indoor

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል የጥምቀት በአልን ስናከብር እርስ በእርስ በመዋደድ ፤ በመተሳሰብ እና በአንድነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም ምዕምናኑ በአሉን ሲያከብሩ በጎ ስራን በመስራት ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

May be an image of 4 people, child, people standing, people sitting and indoor
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም