የደምበል ሀይቅ የከተራ የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የደምበል ሀይቅ የከተራ የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው
ባቱ (ኢዜአ) ጥር 10/2015 የደምበል ሀይቅ የጥምቀት ከተራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
በደምበል ወይም ዝዋይ ሀይቅ አምስት ደሴቶች ያሉት ሲሆን በደሴቶቹ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የታነጹ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት የሚገኙበት ነው።
በዚህ የከተራ በዓል ታቦታቱ ከየደሴቶቹ ወጥተው በአንድ ላይ በመሆን ወደ ማደሪያቸው በታንኳ እየተጓዙ ይገኛሉ።
ምዕመኑ በታንኳ ላይ ሆነው ታቦታቱን ሲያጅቡ ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን እያሳዩ በደምበል ሀይቅ ላይ እየተጓዙ ነው።
የከተራ በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንና የባቱ ከተማ አስተዳደር በጋራ እያስተባበሩት ናቸው።