በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተራ በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተራ በዓል እየተከበረ ነው
ሚዛን አማን (ኢዜአ) ጥር 10/2015 በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተራ በዓል በሀይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ የከተራ በዓል ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።
ከአምስት አድባራት ታቦታቱ በመውጣት ጥምቀት ባህር ወደ ተከተረበት የኮሶኮል ወንዝ በዝማሬና እልልታ እየወረዱ ነው።
በከተማዋ በሁለት ወንዞች ታቦታቱ የሚወርዱ ሲሆን በአማን ክፍለ ከተማ በተመሳሳይ ስድስት አድባራት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች ታጅበው በታላቅ ድምቀት በጋራ ወደ ጥምቀተ ባህር ጉዞ በማድረግ ላይ ናቸው።
በከተማዋ እየተከበረ ያለው የከተራ በዓል በሰንበት ትምህርት ቤቶችና መዝምራን የጋራ ዝማሬ ደምቆ በምዕመናን እየታጀበ ነው።
የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ለማስቻል የማስተባበር ሥራ እየሰሩ ነው።
በተመሳሳይ በቦንጋ፣ ቴፒ እና ተርጫ ከተሞች የከተራ በዓል በድምቀት በመከበር ላይ መሆኑ ተመላክቷል።