ቀጥታ፡

የፓኪስታኑ አሪፍ ሃቢብ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሲሚንቶ፣ በማዳበሪያና ብረታብረት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 9/2015 የፓኪስታኑ አሪፍ ሃቢብ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሲሚንቶ፣ በማዳበሪያና ብረታ ብረት ዘርፎች መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታኑ የአሪፍ ሃቢብ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚ ሞሃመድ ቃሲፍን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም ኮሚሽነሯ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ስላሉ ዕድሎች፣ አማራጮች፣ ማበረታቻዎች እና የሕግ እና ፖሊሲ ማሻሻያዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም የኢንቨስትመንት ከባቢው ለባለሀብቱ አመቺ እንዲሆን ሰፊ ሰራ መሰራቱን ለባለሀብቶቹ አስረድተዋል፡፡

የፓኪስታኑ አሪፍ ሃቢብ ግሩፕ በበኩሉ በኢትዮጵያ በሲሚንቶ፣ በማዳበሪያና ብረታብረት ዘርፎች መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ስራ አስፋጻሚው ሞሃመድ ቃሲፍን መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም