ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጎበኙ

220

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 9/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 'ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝቻለሁ' ሲሉ ገልጸዋል።

'17ሺህ 682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ተሰጥቶናል' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናቸዋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ-ክርስቲያን እየተጠናቀቀ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያስታወቁት።

'የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል' ሲሉም አስታውቀዋል።

ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ አኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምሀርት ይሆነናል ብለዋል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም