የቻን ውድድር የአራተኛ ቀን ውሎ

21


አዲስ አበባ(ኢዜአ) ጥር 8/2015 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ሰባተኛው የአፍሪካ አገራት እግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።


በምድብ አራት ማሊ ከአንጎላ ከምሽቱ 1 ሰአት ፤ በምድብ 5 ከምሽቱ 4 ሰአት ካሜሮን ከኮንጎ ብራዛቪል በሚሉድ ሀዴፊ ስታዲየም ይጫወታሉ።


ትናንት በምድብ ሶስት በተደረገ ጨዋታ ማዳጋስካር ጋናን 2 ለ 1 በማሸነፍ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግባለች።


በዚሁ ምድብ ሞሮኮ ራሷን ከውድድሩ ማግለሏን ተከትሎ ከሱዳን ጋር ልታደርገው የነበረው ጨዋታ ተሰርዟል።


በአገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የቻን ውድድር እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም