ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት - ኢዜአ አማርኛ
ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 8/2015 ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የዕምነቱ ተከታዮች ስፍራዎችን ሲያስውቡ የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ።
በየዓመቱ ጥንቃቄ በጎደለው የማስዋብ ሥራ ወቅት ከኤሌክትሪክ ንክኪ ጋር በሚፈጠሩ አደጋዎች በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እንደሚደርስ አስታውሷል።
የማስዋብ ሥራዎች ለኤሌክትሪክ አደጋ ሊያጋልጡ ስለሚችሉ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊከናወኑ እንደሚባ አገልግሎቱ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ ድንገተኛ የኤሌክትሪክ አደጋ ካጋጠመ በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንዲያሳውቅ አገልግሎቱ አስታውቋል።