በቻን ውድድር ጋና ከማዳጋስካር ይጫወታሉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 7/2015 በአልጄሪያ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 7ኛው የአፍሪካ አገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) ጋና ከማዳጋስካር ዛሬ ከምሽቱ 4 ሰዓት ይጫወታሉ።

በአገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

በምድብ ሶስት ጋና ከማዳጋስካር ከምሽቱ 4 ሰዓት በሞሐመድ ሃምላዊ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጋና እና ማዳጋስካር እርስ በእርሳቸው ሲገናኙ የዛሬው ለአራተኛው ጊዜ ነው።

ሊቢያዊው ሙታዝ ኢብራሂም የሁለቱን አገራት ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

ትናንት በምድብ አንድ ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።

በምድብ ሁለት ሴኔጋል ኮትዲቯርን 1 ለ 0 ስታሸንፍ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ዩጋንዳ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም