በሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 7/2015 ዛሬ ማለዳ በሕንድ በተካሄደው የሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ።

በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ተከታትለው በመግባት የበላይነቱን ይዘዋል።

በውድድሩ አትሌት አንቺዓለም ሃይማኖት 2 ሰአት ከ24 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመግባት አሸናፊ ስትሆን የቦታውንም ክብረወሰን አሻሽላለች።

አትሌት ረሂማ ቱሳ እና አትሌት ለተብርሃን ኃይላይ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል።

በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2 ሰአት ከ7 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ በመግባት አሸንፏል። የቦታውንም ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።

ኬንያዊው አትሌት ፊልሞን ሮኖ ሁለተኛ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኃይሉ ዘውዱ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም