ቀጥታ፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲያካሂደው የቆየውን የባለተሰጥኦ የድምጻውያን ውድድር አጠናቀቀ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 6/2015 የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲያካሂደው የቆየውን የባለተሰጥኦ የድምጻውያን ውድድር አጠናቀቀ።

ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀምበሩ የ3ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በአሸነፊነት አጠናቃለች።

3ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃውያን ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በዚህም ያለምወርቅ ጀምበሩ በአንደኝነት አሸናፊ ሆናለች።

እንዲሁም አሉላ ገ/አምላክ ሁለተኛ፣ ዳንኤል አዱኛ በሦሥተኛ ደረጃ ሲያጠናቅቁ፣ ደሣለኝ አበበ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁት ለእያንዳንዳቸው የ300ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የዓመቱን ሦስት ምዕራፎች በአሸናፊነት ያጠናቀቁ 12 ተወዳዳሪዎችና በልዩ ሁኔታ የተካተቱ ሁለት ተፎካካሪዎች በአጠቃላይ 14 ተወዳዳሪዎች ለ10 ሳምንታት ሲፎካካሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

በዚህም አራት ተወዳዳሪዎች ተለይተው በዛሬው ዕለት ደሳለኝ አበበ፣ አሉላ ገ/አምላክ፣ ዳንኤል አዱኛ እና ያለምወርቅ ጀምበሩ የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ ለመሆን ብቃታቸውን ሲያሳዩ ውለዋል፡፡

በርካታ ተመልካቾችና አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት በቀጥታ ስርጭት በተካሄደው የፍጻሜ ውድድርም አሸናፊዋ መለየቷን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም