ቀጥታ፡

በ12ኛው የሚዲያ ካፕ የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ፕራይም ሚዲያን 5 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) በ12ኛው የሚዲያ ካፕ የመክፈቻ ጨዋታ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የፉት ሳል ቡድን የፕራይም ሚዲያ አቻውን 5 ለ 2 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ።

“አዝናኙ ሲዝናና” ሚዲያ ካፕ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ተጀምሯል።

በውድድሩ መክፈቻ በተደረገው ጨዋታ በምድብ አንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የፉት ሳል ቡድን የፕራይም ሚዲያ አቻውን 5 ለ 2 ረቷል።

በጨዋታው የኢዜአው ይሁን ይታይህ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ በመስራት የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ሲመረጥ ከአዘጋጆቹ የስፖርት ትጥቅ ተሸላሚም ሆኗል።

በውድድሩ መክፈቻ ቀን በምድብ ሁለት በተደረገ ጨዋታ ብስራት ኤፍ ኤም ባላገሩ ቲቪን 5 ለ 1 እንዲሁም በምድብ አምስት ኢትዮፒካል ሊንክ ሞዛይክ ስፖርትን 7 ለ 4 አሸንፈዋል።

12ኛው የሚዲያ ካፕ መርሐ-ግብር ነገም ቀጥሎ ይውላል።

አጠቃላይ ለውድድሩ 100 ሺህ ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ ቡድኖች በቅደም ተከተል የ25፣ 15 እና የ10 ሺህ ብር ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በስድስት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄደው 12ኛው ሚዲያ ካፕ ውድድር እስከ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም