ቀጥታ፡

የደቡብ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው

አርባ ምንጭ (ኢዜአ) ጥር 06/2015 በደቡብ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ መክፈቻ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬሕይወት አበበ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የክልሉ የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ መገኘታቸው ተመላክቷል። 

በንቅናቄ መድረኩ የደቡብ ክልል የ10 ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ሪፖርትና እና የ2015 ዓ.ም የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም