ወጣቶች የተገኘውን ሰላም ተጠቅመው ራሳቸውንና አገራቸውን ለመለወጥ መስራት ይኖርባቸዋል-አቶ አሻድሊ ሃሰን - ኢዜአ አማርኛ
ወጣቶች የተገኘውን ሰላም ተጠቅመው ራሳቸውንና አገራቸውን ለመለወጥ መስራት ይኖርባቸዋል-አቶ አሻድሊ ሃሰን
አሶሳ (ኢዜአ) ጥር 6/2015 ወጣቶች የተፈጠረውን ሰላምና መረጋጋት ተጠቅመው በሙሉ አቅማቸው በመስራት ራሳቸውንና አገራቸውን ለመለወጥ መትጋት እንደሚገባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
"የሰላም ልማት እና ዴሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ውይይት በአሶሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አቶ አሻድሊ ሀሰን ወጣትነት የልማት ኃይል ነው፤ ወጣቶች በዘመናቸው የሚያሳልፉትን ተግባር የሕይወታቸው መሠረት ነው” ብለዋል።
አሁን በክልሉ የተገኘውን ሰላም በመጠቀም የተፈጥሮ ሃብትን በሚገባ በማልማት ራሳቸውንና አገራቸውን ለመቀየር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀጂራ ኢብራሂም በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና የክልሉን ሰላም እንዲመለስ ከፍተኛ መስዋዕትነት ተከፍሏል።
በዚህም አስተማማኝ ሰላም እየመጣ ነው ብለዋል።
የአንድ አገር ዘላቂነት የሚለካው ባላት ሃብት ሳይሆን አስተማማኝ ሰላም ሲኖራት ነው ያሉት ኃላፊዋ የትውልድ ቅብብሎሽን ለማጠናከር ወጣቱ ሰላምን በማጠናከር ተሳትፎውን ማስቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።