ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 4/2015 የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባኤርቦክ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪ ኮሎናን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዚህም የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር በነበራቸው ውይይት፤ የአገራቱን ረጅም ዘመን የዘለቀ ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በመንግስትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሚደረገው መልሶ ግንባታ ተግባራት ሁለቱ ሀገራት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሮቹ አረጋግጠዋል።
የመልሶ ማቋቋም እና የመደገፍ ስራዎች ሴቶችን ታሳቢ በማድረግ ላይ ያተኮሩ መሆን እንዳለባቸው በውይይታቸው ተነስቷል።