ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አልጄሪያ አመራ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 3/2015 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ሰባተኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ውድድሩ ስፍራ አቅንቷል።

በአገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ከነገ በስቲያ ይጀመራል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።

በአገር ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ እንዲሁም ከአገር ውጪ በሞሮኮ ለሰባት ቀናት ሲዘጋጅ ቆይቷል።

May be an image of 6 people, people standing, indoor and text

የመጨረሻ ልምምዱንም ትናንት በካዛብላንካ በሚገኘው ላርቢ ዛውሊ ስታዲየም አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ የሞሮኮ ቆይታውን አጠናቆ ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ አልጄሪያ አምርቷል።

ዋልያዎቹ በቻን ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ አልጄሪያ እንዲሁም ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር ተደልድለዋል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን የፊታችን ቅዳሜ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት በስታድ ዲ ባራኪ ከሞዛምቢክ ጋር ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም