ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 3/2015 የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር በወጣቶቹ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት "ዛሬ የከተማችን አዲስ አበባ ድምቀትና ጌጥ ከሆኑት የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ጋር በወጣቶቹ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙርያ ተወያይተናል” ብለዋል።

በጋራ ከተማችንን ስለምናለማበት ሁኔታ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉም ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት፡፡

May be an image of one or more people and people standing

“በስፖርት ማዘውተርያ ቦታዎች፣ በስራ እድል ፈጠራና በመልካም አስተዳደር ዙርያ ወጣቶቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ወስደን የሚታረመውን አርመን፤ የሚስተካከለውን አስተካክለን በጋራ ለመፍትሄው እንደምንረባረብ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁም” ብለዋል ፡፡

አክለውም የአዲስ አበባ ወጣቶች ሃሳባቸውን በሰለጠነና በሰከነ መንገድ የሚያንፀባርቁ እንጂ በአመፅ ወይንም የሌላ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደማይፈልጉ አረጋግጠዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከሌሎች የከተማችን ወጣቶች ጋር ተከታታይ መድረኮችንና ውይይቶችን ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም