ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 2/2015 የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ከሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ እና የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጄነራል አህመድ ሞአሊን ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

በመርሃ-ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ እና የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ፈርዶውሳ ኦስማን ተገኝተዋል።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት ከፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ግንኙነት ባለፈ በኢኮኖሚ ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ስምምነቱ ሁለቱ አገራት በዘርፉ ያላቸውን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

የሶማሊያ የትራንስፖርትና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ፋርዶውሳ ኦስማን በበኩላቸው፤ ስምምነቱ በትራንስፖርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ ለመውሰድ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is image-75.png

ሁለቱ ሀገራት በሲቪል አቪዬሽን ዙሪያ የሚያደርጉትን የሁለትዮሽ ትብብር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም