ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 30/2015 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል የደም ልገሳ ማድረጋቸው ተገለጸ።

የተቋሙ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አመራርና አባላት “ደማችን ለወገናቸን” በሚል መሪ ሀሳብ ልገሳውን ያደረጉት በድሬዳዋ ከተማ ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራር እና አባላት በሕዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ሕግ የማስከበር ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን ተቋሙ ገልጿል።

ከዚሁ ኃላፊነታቸው ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸው አባላት በደም እጦት ምክንያት ለከፋ ጉዳት እንዳይጋለጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የደም ልገሳ በራሳቸው ተነሳሽነት ማድረጋቸው ተመልክቷል።

May be an image of 4 people, people sitting and military uniform

ደም ከለገሱት መካከል ኢንስፔክተር ገነት ብርሃኔ ‘’እኛ ወደ ፖሊስ ስንቀላቀል አንዱ አካላችን ለሆነው ሕዝባችን ውድ ሕይወታችን ጭምር ለመስጠት ቃለ-መሃላ ፈጽመናል፤ ከዚህ አንጻር ደም በመስጠት የወገናችንን ሕይወት ማዳን ለእኛ ቀላሉ ነገር ነው’’ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት ከዚህ በፊትም በተለያዩ ወቅቶች የወገናቸው ሕይወት እንዳያልፍ የደም ልገሳ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም