ካለን ማካፈል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችንን የምናሳይበት ነዉ- የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም - ኢዜአ አማርኛ
ካለን ማካፈል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችንን የምናሳይበት ነዉ- የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 29/2015 ካለን ማካፈል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችንን የምናሳይበት ነዉ ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብራሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡
የገናን በዓል በማስመልከት በብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አካባቢ ላሉ 120 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
የኢፌድሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር "ያለንን ማካፈል የኖርንበት የኢትዮጲያዊነት ባህላችንና እንደ ተቋም ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችንን የምናሳይበት ነዉ" ብለዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰራዊታችን ለሃገር ሰላም ሲል ውድ ህይወቱን የሚገብር ፤ ህዝቦቿ ሲቸግሩ ካለው የሚያካፍል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ ነው ሲሉም አክለዋል።
ሰራዊታችን የሰላማችን ዘብ የቸገረን ጊዜ ረዳታችን ነው፤ የገናን በዓል በማስመልከት ለተደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ ድጋፍ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ድጋፉን የ40ኛ ዙር 1ኛ ብርጌድ ተመራቂ የኮማንዶ አባላት ያሰባሰቡ ሲሆን ከወላይታ ዞን እና ሲዳማ ክልል ውስጥ ካሉ 5 ቀበሌዎች ለተውጣጡ ከ120 በላይ ነዋሪዎች የተበረከተ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።