የሚሲዮን መሪዎች የመከላከያ ሚኒስቴርን ማሻሻያ የሚያግዝ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል- ዶክተር አብረሃም በላይ - ኢዜአ አማርኛ
የሚሲዮን መሪዎች የመከላከያ ሚኒስቴርን ማሻሻያ የሚያግዝ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል- ዶክተር አብረሃም በላይ
ታኀሣሥ 27/2015 (ኢዜአ) በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በመከላከያ ሚኒስቴር እየተተገበረ ያለውን ማሻሻያ የሚያጠናክር ስራ መስራት እንዳለባቸው የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ለውጭ ጉዳይ የስራ ሀላፊዎች እና ለሚሲዮን መሪዎች በተቋሙ እየተተገበረ ስላለው የሪፎርም ስራ ገለፃ አድርገዋል ።
በገለጻቸው ኢትዮጵያን ወክለው ወደ ተለያዩ አገራት የሚሄዱ አምባሳደሮች የአገር መከላከያ ሰራዊቱ በአካል ፣ በእውቀት ፣ በትጥቅ ፣ በመረጃና በቴክኖሎጂ የላቀ እንዲሆን አስፈላጊውን እገዛ እንዲደረግ ብርቱ ስራ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል።
መድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ገለፃውን መነሻ በማድረግም ውይይት መካሄዱን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።