በቻይና በኤችአይቪ ኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ14 ከመቶ ጨምሯል

መስከረም 22/2011 ቻይና በኤችአይቪ ኤድስ የሚያዙ ዜጎቿ ቁጥር በ14 በመቶ መጨመሩን አስታወቀች፡፡ ቢቢሲ በጤና አምዱ ይዞት በወጣው ዘገባ እንዳመለከተው 820 ሺህ ዜጎቿ በኤች አይቪ ተይዘዋል፤ሃገሪቱ የጤና ባለስልጣናት እንዳሉት 40 ሺህ ያህሉ እ.ኤ.አ በ2018 ሁለተኛው ሩብ ዓመት የተያዙ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከበፊቱ ባልተለመደ ሁኔታ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የተያዙ ናቸው፡፡ ከዓመት ወደ ዓመት አዲስ በኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ100 ሺዎች እየጨመረ መሆኑን በቻይና ዩዋን ግዛት በተካሄደ ኮንፍረንስ ላይ መገለፁን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ አብዛኛው የበሽታው መተላለፍ መንስኤ ያለበቂ ጥንቃቄ የሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት መሆኑን የገለጸው ዘገባው የቻይና መንግስት እ.ኤ.አ ከ2003 ጀምሮ ኤችአይቪን መከላከል የሚያስችለውን ዓለም አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ ህክምናን ለመተግበር ቃል መግባቷን ዘገባው አስታውሷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም