ቀጥታ፡

ወላይታ ዲቻ በቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ(ኢዜአ) ታህሳስ 26/2015 በደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ አዲስ አበባ ፖሊስን በማሸነፍ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

የፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በሮቤ ስታዲየም ተደርጓል።

የሊጉ መሪ ወላይታ ዲቻ አዲስ አበባ ፖሊስን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ዲቻ ነጥቡን ወደ ስምንት ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል።

በሌሎች ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ ከተማ መቻልን 3 ለ 0 እንዲሁም ሙገር ሲሚንቶ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 1 አሸንፈዋል።


በሮቤ ስታዲየም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ሳምንት ሲከናወኑ የቆዩት የቮሊቦል ፕሪሚየር ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜውን አግኝተዋል።


ከአራተኛ እስከ ሰባተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር በየካቲት ወር 2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም