የጨርቃ ጨርቅ አውደ ርዕይ አዳዲስ የገበያ ትስስር እየፈጠረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጨርቃ ጨርቅ አውደ ርዕይ አዳዲስ የገበያ ትስስር እየፈጠረ ነው
አዲስ አበባ መስከረም 21/2011 የአፍሪካ የጥጥ፣ ጨርቃ ጨርቅ አልባሳት፣ የቤት ውስጥ ማሳመርና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ አውደ ርዕይ አዳዲስ የገበያ ትስስሮችን እየፈጠረላቸው መሆኑን ተሳታፊዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ አውደ ርዕይና ጉባኤ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል። አውደ ርዕይው ለኢትዮጵያውያን አምራችና ሻጮች ከአፍሪካና አለም አገሮች ጋር የልምድና የገበያ ትስስሮች ለመፍጠርና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያለመ ነው። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአውደ ርዕይው ተሳታፊዎች ቀደም ሲል በተካሄዱት ሶስት አውደ ርዕዮች ከተለያዩ አምራችና ሻጮች ጋር የመገናኘት እድል አግኝተዋል። በዚህም በተለያዩ አገሮች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን ጨምሮ እውቀትና ልምዶችን ማግኘት አስችሏቸዋል።
ተሳታፊዎች እንደሚሉት፤ በአገር ውስጥና በውጭም የተለያዩ የገበያ መዳረሻዎችን ከማግኘት በተጨማሪ የምርት ግብዓቶችንም በአንድ ቦታ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። በአዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃ ጨርቅ አምራችነት የተሰማራው ኬጅጅ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና የደቡብ አፍሪካ የቆዳ ውጤቶች አምራች ኩባንያ በበኩላቸው ከኢትዮጵያውያንና ሌሎች አገሮች አዳዲስ የገበያ ትስስሮችን እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሶስት አውደ ርዕዮች ለኢትዮጵያውያን አምራቾች የገበያ ትስስርና የልምድ ልውውጦች መገኘታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የተለያዩ የውጭ ባለሃብቶች ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው እንዲያመርቱ "እድል ፈጥሯል" ይላሉ። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቦጋለ በለጠ እንዳሉት፤ የዚህ አውደ ርዕይ ዓላማ የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት ለዓለም ማስተዋወቅ እንዲሁም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ ነው። በአውደ ርዕይው ጅምላ ሻጮች፣ ቸርቻሪዎችን ጨምሮ በጨርቃ ጨርቅ፣ ቆዳ ውጤቶችና ሌሎች የማምረቻ ዘርፎችና ቴክኖሎጂ አቅራቢነት የተሰማሩ ይገኛሉ። ለአራት ቀናት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ከ250 በላይ ዓለም አቀፍ አምራችና ለውጭ ገበያ አቅራቢዎች፣ ከአራት ሺ በላይ ከተለያዩ አለም አገሮች የተውጣጡ ነጋዴዎችና ገበያ አፈላላጊዎች ይሳተፋሉ። አውደ ርዕይው በሜሴ ፍራንክፈርት ኤግዚቢሽን፣ በጂ ኤም ቤ ኤች፣ በኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበርና በኢትዮጵያ መንግስት አማካኝነት የተዘጋጀ ነው።