ቀጥታ፡

“የኢትዮጵያ ታምርት” አገር አቀፍ ንቅናቄ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው

ሐረር(ኢዜአ) ታህሳስ 22/2015  የኢትዮጵያ ታምርት  አገር አቀፍ የኢንዱስትሪ ንቅናቄ አካል የሆነ ውይይት በሐረር ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሀመድን፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በእለቱም የኢትዮጵያ ታምርት መርሃ ግብር መጀመር በአገር አቀፍ ደረጃ በኢንዳስትሪው ዘርፍ በርካታ ውጤት ማስገኘቱ ተመልክቷል።

በተለይ ማምረት ያቆሙ ኢንዳስትሪዎች ወደ ምርት እንዲገቡ፣ በማምረት ላይ ያሉ ደግሞ ምርታቸው እንዲጎለብት ማስቻሉን እንዲሁ።

በመድረኩ የ2015 በጀት አመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመርሃ ግበሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም