የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በረራ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በረራ ይጀምራል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 20/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽሬ ከተማ በቀን አንድ በረራ እንደሚጀምር ገለጸ።
አየር መንገዱ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ጊዜ ከፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምርም ነው አየር መንገዱ በማህበራዊ የትስስር ገጹ የገለጸው።
በመሆኑም ደንበኞቻችን ባሉበት ቦታ ሆነው ድረ ገፃችንን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችንን ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን ብሏል።