ቀጥታ፡

"የኢትዮጵያ ታምርት" አገር አቀፍ ንቅናቄ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

ድሬደዋ ታህሳስ 20/2015 ''የኢትዮጵያ ታምርት'' አገር አቀፍ የኢንዱስትሪ ንቅናቄ አካል የሆነ ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈትሂያ አደን፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የ2015 በጀት አመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዕቅድ እና አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም