ቀጥታ፡

በሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል እየተከበረ ነው

ሀዋሳ (ኢዜአ)  ታህሳስ 19/2015  በሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በደማቁ እየተከበረ ነው።

 በየዓመቱ ታህሳስ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊው የንግስ በዓል በሀዋሳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ታጅቦ እየተከበረ ነው ።

በክብረ በዓሉ ሥነ ሥርዓት ላይ  የሲዳማ  እንዲሁም የጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ የከምባታ፣ ሀዲያ እንዲሁም ስልጤ እንዲሁም  የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ህርያቆስ ተገኝተዋል።

እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና እንግዶች የተገኙ ሲሆን በክብረ በዓሉ ላይ የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በተጨማሪ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ከሀገር ውጭ የመጡ ምዕመናንም በክብረ በዓሉ ላይ በልብሰ ተክህኖ እና በውብ ሀገራዊ አልባሳት አሸብርቀው ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም