ቀጥታ፡

አየር መንገዱ ነገ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራውን ይጀምራል

አዲስ አበባ ኢዜአ ታህሳስ 18/2015 ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከነገ ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራውን ማድረግ እንደሚጀምር አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ ለኢዜአ እንደገለጹት አየር መንገዱ ተቋርጦ የነበረውን የመቀሌ መደበኛ በረራ በነገው እለት ይጀምራል።

ከጥቂት ሣምንታት በፊት አየር መንገዱ ወደ ትግራይ ክልል ዳግም በረራ ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑን ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም