ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ(ኢዜአ) ታህሳስ 16/2015 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፌደራል ማረሚያን በማሸነፍ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበት ድል ማስመዝገብ ችሏል።
የአራተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐግብር ዛሬ ተጀምሯል። በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም አንድ ጨዋታ ተደርጓል።
የሊጉ መሪ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፌደራል ማረሚያን 42 ለ 29 ረቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን ወደ ስምንት ከፍ በማድረግ መሪነቷን አጠናክሯል። ክለቡ አስከ አሁን ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች አሸንፏል።
የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ቀጥሎ ሲውል ፋሲል ከነማ ከሚዛን አማን ከተማ ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ20፤ መቻል ከከምባታ ዱራሜ ከረፋዱ 3 ሰአት ከ40 ይጫወታሉ።
የፕሪሚየር ሊጉ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ ይታወቃል።
ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ እንደሚደረጉም ገልጿል።