የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አቅም ከፍተኛ ነው --ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አቅም ከፍተኛ ነው --ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ታህሳስ 16/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማምረት ላይ ከተሠማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መካከል አንዱን መጎብኘታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አቅም ከፍተኛ ነው ብለዋል።

"በአማራ ክልል በኮምቦልቻ ከተማ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማምረቻ ላይ ከተሠማሩት ደፋር ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መካከል አንዱን ጎብኝተናል" ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ታምርት ላይ መሠማራት ለማንኛውም ባለሀብት አዋጭ የሆነ ሥራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አመላክተዋል።