የገዳ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የገዳ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 15/2015 የገዳ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ የአገሪቱን የብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች በማሟላት በዛሬው እለት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።
የማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ባንኩ በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ ባስገነባው ህንጻ እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወልዴ ቡልቱ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ባንኩ ከ28 ሺህ በሚበልጡ ባለ አክሲዮኖች 552 ሚሊየን የተከፈለ ካፒታል ይዞ ወደ ሥራ ገብቷል።
ባንኩ በሰላሳ ቅርንጫፎች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
ባንኩ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።