ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በብላቴ ወንዝ ተፋሰስ የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም እየለማ ያለ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻን ጎበኙ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 14/2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በብላቴ ወንዝ ተፋሰስ የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም እየለማ ያለ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "በአንድ ወቅት ምንም ልማት ባልነበረበት የብላቴ ወንዝ ተፋሰስ፣ የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎች እየተንዠረገጉበት ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"በቆራጥ የግሉ ሴክተር ባለሀብቶች የሚለሙትን እርሻዎች የምርታማነት ዐቅም ለማየት ወደ ቦታው ተመልሰናል" ነው ያሉት።

የአካባቢው ምርታማነት ከክፍፍል ይልቅ ትብብር የሚያስገኘውን ውጤት ማሳያ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ተሞክሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ መስፋፋት አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም