ቀጥታ፡

በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሔደ

አዲስ አበባ ኢዜአ ታህሳስ 14/2015፦ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት በናይሮቢ ተካሔደ።

በውይይቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የህወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ ተገናኝተዋል።

የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካዩች የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ በተገኙበት የስምምነቱ አፈጻጸም ላይ ውይይት መካሔዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም