ቀጥታ፡

የሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ዑመር-ጊኒር መገንጠያ የአስፓልት መንገድ ኘሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ እየተካሄደ ነው

ሮቤ ታህሳስ 13/2015 (ኢዜአ) የሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ዑመር-ጊኒር መገንጠያ የአስፓልት መንገድ ኘሮጀክት ግንባታ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀመር።

በማስመጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሚገነባው መንገድ 120 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ለሆነው ሶፍ ዑመር ዋሻ ጭምር ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚወጣበትና የግንባታ ጊዜውም ሶስት ዓመት መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም