የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የገዢው ፓርቲ ኤ ኤን ሲ መሪ በመሆን በድጋሚ ተመረጡ

አዲስ አበባ ታኅሳስ 10/2015 (ኢዜአ) ፦የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ገዢውአፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ(ኤ.ኤን.ሲ) ፓርቲን በድጋሚ እንዲመሩ ተመረጡ።

ፕሬዚዳንት ራማፎሳ በሁለተኛ ዙር እንደሚያሸንፉ ከምርጫው በፊት ሰፊ ግምት ተሠጥቷቸው እንደነበር የፓርቲውን ኃላፊዎች ጠቅሶ የዘገበው ኤንቢሲ ነው።

በፓርቲው ስር ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ በሚል እውቅና ከተሰጣቸው ሌሎች እጩዎች ከፍተኛውን ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውም በመረጃው ተመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሁን የገዢው ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ፓርቲውን የሚመሩ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም