ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ምርጥ የአፍሪካ ጉምሩክ ኮሚሽነር በመባል ዕውቅና ተሰጣቸው - ኢዜአ አማርኛ
ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ምርጥ የአፍሪካ ጉምሩክ ኮሚሽነር በመባል ዕውቅና ተሰጣቸው

ታኅሳስ 07/2015(ኢዜአ) የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ምርጥ የአፍሪካ ጉምሩክ ኮሚሽነር በመባል እውቅና ተሰጣቸው።
የአፍሪካ ምርጥ የመንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሽልማት አዘጋጅ ድርጅት የሆነው አፍሪካን ፐብሊክ ሰርቪስ ኦፕቲመም አዋርድ አህጉር አቀፍ የተቋማት ልዩ የሽልማት መርሐግብር በጋና አክራ አካሂዷል።
በዚህም የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በመላው አፍሪካ ካሉ የጉምሩክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ምርጥ የአፍሪካ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እውቅና አግኝተዋል፡፡
ኮሚሽነር ደበሌ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ከሚሽን በእርሳቸው አመራር በርካታ እውቅናዎችን እንዲያገኝ በማድረጋቸው እና ምርጥ ውሳኔ ሰጪ አመራር በመሆናቸው ዕውቅናው መስጠቱ በመርሐግብሩ ላይ ተመላክቷል።
ኮሚሽነር ደበሌ ሽልማቱን በጋና ዋና ከተማ አክራ ተገኝተው መረከባቸውንና ከሽልማቱ ጎን ለጎን የአፍሪካ መንግስታዊ ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ የሚመክር ጉባዔ መካሄዱን ከፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።