ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊሳዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊሳዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2015(አዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊሳዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መስማማታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ዶክተር ፋሃድ ኦባይዱላህ አል-ሁመይዳኒን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ከአምባሳደሩ ጋር ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና የሁለቱን ሀገራት ፖሊሳዊ ግንኙነት አጠናክረው በማስቀጠል አብሮ ለመሥራት መክረዋል።
አምባሳደር ዶክተር ፋሃድ ኦባይዱላህ አል-ሁመይዳኒ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የድንበር ቁጥጥር አደረጃጀትን በሎጂስቲክስ እና በአቅም ግንባታ ለመደገፍ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ኅብረትን ለማገዝ ቃል ገብተዋል።
አምባሳደሩ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የምሥራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ኅብረት ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸውም “እንኳን ደስ አለዎት” ማለታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።