በአሜሪካ ኦሃዮ የሆኖሉሉ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ

158

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 3/2015 በአሜሪካ ኦሃዮ የሆኖሉሉ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸንፈዋል።

በኦሃዮ ግዛት ሆኖሉሉ የባህር ዳርቻ በተካሄደው 50ኛው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቀዳሚነት አጠናቀዋል።

በውድድሩ አትሌት አሰፋ መንግስቱ 2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ አንደኛ በመሆን አጠናቋል።

ኬኒያዊው በርናባስ ኪፕቱም እና ጃፓናዊው ዩሂ ያማሽታ ሁለተኛና ሶሰተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል።

በሴቶች መካከል በተደረገው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሳየች አያሌው 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ 58 ሴኮንድ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቀቅ ሌላኛዋ አትሌት አበበች አፈወርቅ 2 ሰዓት ከ34 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ በመግባት 2ኛ ሆናለች።

በውድድሩ ጃፓናዊቷ ኤሪ ሱዝኪ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።

በዚህ ውድድር በቀዳሚነት ያጠናቀቁት አትሌቶች እያንዳንዳቸው 25 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም