የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና ገበያ እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና ገበያ እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለጸ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ታህሳስ 3/2015 የቻይና መንግሥት ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና ገበያ እንዲገቡ መፍቀዱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የቻይና መንግስት የኢትዮጵያ ምርቶች በቻይና ገበያ ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፍቀዱን አመልክቷል።
በአጠቃላይ ንግድ በሚነገድባቸው 6 ሺህ 422 ምርቶች ውስጥ 1 ሺህ 644 ምርቶች ከቀረጥና ኮታ ነጻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
ይህ የገበያ እድል በአንድ ወገን (በቻይና በኩል) በመሰጠቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ምንም አይነት ግዴታ እንደማይኖር ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡