አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ታህሳስ 2/2015 በፊልም ሥራዎቹ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የፊልም ባለሙያ የሆነው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ባደረበት ሕመም ለሳምንታት በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።

አርቲስት ታሪኩ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም