ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የምሥራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆኑ

23

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሕዳር 29/2015 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት (EAPCCO) ፕሬዝዳንት ሆኑ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ24ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና ኢንስፔክተር ጀነራል ዲዩዶኔ አሙሊ ባሂግዋ ለኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ሃላፊነታቸውን አስረክበዋል፡፡

በዚህም ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የምሥራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም