17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀዋሳ ስታዲየም እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀዋሳ ስታዲየም እየተከበረ ነው

ሀዋሳ ህዳር 29/2015 (ኢዜአ) 17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በበአሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች፣ ከንቲባዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በበአሉ ላይ ታድመዋል።
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮችም በበአሉ ላይ ተገኝተዋል።

ህጻናትና ወጣቶች የተለያዩ ትርኢቶችን እያቀረቡ ሲሆን የሀገር መከላከያ ማርሽ ባንድም የተለያዩ ጣእመ ዜማዎችን በማቅረብ ለበአሉ ድምቀት እየሰጠ ይገኛል።
17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተከበረ ነው።