ቀጥታ፡

17ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ በሀዋሳ እየተከበረ ነው

ሀዋሳ ህዳር 29/2015 (ኢዜአ) የዘንድሮው 17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ''ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም'' በሚል ቃል በሀዋሳ እየተከበረ ነው።

በአሁኑ ሰዓት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርች ባንድ ለዕለቱ ክቡር እንግዳ የክብር ሠላምታ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በዓሉ ላይ የሚካፈሉ በሀገሪቱ ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች በሀዋሳ አለም አቀፍ እስታዲየም ታድመዋል።

ህጻናትና ወጣቶች የተለያዩ ትርኢቶችን እያቀረቡ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የሚታደሙ የሀይማኖት አባቶች የሲቪክ ማህበራት ተወካዮችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም