በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ላይ ለመታደም የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች፣ ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሀዋሳ እየገቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ላይ ለመታደም የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች፣ ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሀዋሳ እየገቡ ነው
ሀዋሳ ህዳር 28 /2015 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ነገ በሚከበረው 17ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ላይ ለመታደም የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች ፣ ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሀዋሳ ከተማ መግባት ጀምረዋል ።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጅሉ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፤ የሱማሌ ክልል ርእስ መስተዳድር ሙስጣፌ ሙሃመድ፣ የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢኒጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ሀዋሳ ገብተዋል ።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ጨምሮ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትም ሀዋሳ ገብተዋል።
እንግዶቹ ሀዋሳ ከተማ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ነገ በሀዋሳ ከተማ ለሚከበረው 17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዝግጅት መጠናቀቁን የሲዳማ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ መግለጻቸውን ኢዜአ መዘገቡ ይታወቃል።